歌曲 / 歌词

Hedetch alu

Listen on Apple Music

歌词

ትላንትና ማታ አሃ በደጅሽ አልፌ
ልቤን ትቼ መጣሁ ሳንባዬን ታቅፌ
ምነው ባደረገኝ የደጅሽን አፈር
አንቺ ስትረግጪኝ እኔ እንድንፈራፈር
እኔ እንድንፈራፈር
ሄደች አሉ ከቤቴ በላይ አይኗን ሳላይ
ከጥንት ነው ከመሰረቱ
እፍን እፍን ይወዳል ቤቱ
ከመልክተኛውም አለው ገደ-ቢስ
የለችም ይለኛል ከደጇ ሳይደርስ
በስማም በስማም አልኩኝ ሴጣኑን ፈርቼ
ብዙ የለመድኩት ብቻዬን ቀርቼ
ብቻዬን ቀርቼ
አወይኔ ወይኔ ዘንድሮ
ካንቺ መለየቴ ሆነብኝ እሮሮ
ሆነብኝ እሮሮ
እኔ ራሴን አሞኝ ተኝቼ በአልጋ ላይ
ወዴት ትሄጃለሽ ሞት ሽረቴን ሳታይ
ታመሽ ታምሚያለሁ ሲያደክሙሽ ደም ወጣኝ
ስትሞች ግን አልሞትም ደሃው ምን በወጣኝ
ደሃው ምን በወጣኝ
ሄደች አሉ ከቤቴ በላይ አይኗን ሳላይ
ሄደች አሉ ጋራ ጋራውን ነፋሻውን
ትላንትና ማታ አሃ በደጅሽ አልፌ
ልቤን ትቼ መጣሁ ሳንባዬን ታቅፌ
ምነው ባደረገኝ የደጅሽን አፈር
አንቺ ስትረግጪኝ እኔ እንድንፈራፈር
እኔ እንድንፈራፈር
ሄደች አሉ ከቤቴ በላይ አይኗን ሳላይ
ከጥንት ነው ከመሰረቱ
እፍን እፍን ይወዳል ቤቱ
ከመልክተኛውም አለው ገደ-ቢስ
የለችም ይለኛል ከደጇ ሳይደርስ
እኔ ራሴን አሞኝ ተኝቼ በአልጋ ላይ
ወዴት ትሄጃለሽ ሞት ሽረቴን ሳታይ
ታመሽ ታምሚያለሁ ሲያደክሙሽ ደም ወጣኝ
ስትሞች ግን አልሞትም ደሃው ምን በወጣኝ
ደሃው ምን በወጣኝ
ኦሆሆ ኦሆሆ ኦሆሆ